የአንበጣ ወረርሽኝን ለመከላከል 41 ሺህ 500 ሊትር ኬሚካል ማሰራጨቱን የግብርና ሚኒስቴር አስታወቀ።
በግብርና ሚኒስቴር የዕፅዋት ጥበቃ መሪ ሥራ አስፈፃሚ የሆኑት አቶ በላይነህ ንጉሴ በክልሎች የተከሰተውን የአንበጣ መንጋ ወረርሽኝ በሰብል ላይ የከፋ ጉዳት እንዳያደርስ በሚደረገው የመከላከል ሥራ በቂ የኬሚካል ክምችት ባይኖርም ያለውን ችግር ሊቋቋም የሚችል የኬሚካል ክምችት እንዳለ ጠቁመዋል።
የአንበጣው ወርርሽኝን የማጥቃት ደረጃው እየተጠና ኬሚካል መርጨት የሚያስፈልገውን የመለየት ሥራ እየተሰራ መሆኑን ገልፀዋል።
ተቋሙ የአንበጣ ወረርሽኝና ፀረ ሰብል ተባዮችን ለመከላከል ከባለድርሻ አካላት ጋር በቅንጅት እንደሚሰራ አመላክተዋል።
በማህሌት አማረ
2023-08-15
