በአማራ ክልል በተወሰነው የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ አፈፃፀም ሂደት በዋነኝነት ህግ ማስከበር የክልሉን ሰላም መመለስ ላይ ያተኮረ መሆኑን ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትርና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አቶ ደመቀ መኮንን ገለፁ።
አቶ ደመቀ መኮንን ይህን የገለፁት መቀመጫቸውን አዲስ አበባ ላደረጉ አምባሳደሮች፣ ዲፕሎማቶችና የዓለም አቀፍ ድርጅቶች ኃላፊዎች በወቅታዊ ጉዳዮች ዙሪያ ማብራሪያ ሲሰጡ ነው።
ከተለያዩ የህብረተሰብ ተወካዮች ጋር ውይይት በማድረግ መሰረታዊ አገልግሎቶች እንዲጀመሩ፣ ንፁሃን ዜጎች ከአደጋ አንዲጠበቁና በክልሉ ህግ እና ስርዓት እንዲከበር እየተሰራ መሆኑን ተገልጿል።
የፍትህ ሚኒስትርና የአስቸኳይ ጊዜ ጠቅላይ መምሪያ አባል ዶክተር ጌዲዮን ጢሞቲዎስ የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ አፈፃፀም ሂደትና እና የተገኙ ውጤቶችን አስመልክተው ለዲፕሎማቶችና ዓለም አቀፍ ማህበረሰብ በወቅታዊ ጉዳይ ላይ ገለጻ አድርገዋል።
በሰፍራው የመንግስት ፅኑ ፍላጎት በአገሪቱ እና በክልሉ ሰላምን ማረጋገጥ እንደሆነ የተገለፀ ሲሆን በውይይቱ ወቅት በቀረቡ ጥያቄዎች ዙሪያ ምላሽ እና ማብራሪያ መሰጠቱን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ዘግቧል።
በብሩክታዊት አስራት
2023-08-16
