ሀገሬ ቲቪ

የኬንያ የውጪ ብድር መጠን በያዝነው ዓመት ብቻ 10 ቢሊዮን ዶላር ደርሷል ተባለ።

የኬንያ የውጪ ብድር መጠን በያዝነው ዓመት ብቻ 10 ቢሊዮን ዶላር ደርሷል ተባለ።

ይህም በሀገሪቱ ታሪክ ከፍተኛው ነው ተብሏል።

የኬንያው ፕሬዝዳንት ዊሊያም ሩቶ ወደ መንበረ ሥልጣን በመጡበት ዓመት ከፍተኛ ገንዘብ ከውጪ መበደራቸው ተዘግቧል።

የዊሊያም ሩቶ መንግሥት በዚህ ዓመት ተበድሮታል ከተባለው ገንዘብ ውስጥ ወደ 92 በመቶ የሚሆነው ባለፉት 9 ወራት ብቻ የተመዘገበ ነው ተብሏል።

ኬንያ በዚህም ሳቢያ አጠቃላይ የዕዳ ክምችቷ በ10.8 ቢሊዮን ዶላር ከፍ ብሏል።

ኬንያ ያለባት የውጪ ብድር እዳ መጠን 37.5 ቢሊየን ዶላር መድረሱን መረጃዎች ያመለክታሉ።

በሳምሶን ገድሉ
2023-08-16