ሀገሬ ቲቪ

ሕዝባዊ አመጽ ሊፈጥር የሚችለው የምግብ ዋጋ መናር

የአፍሪካ ሀገራት ሌላ ከባድ እና ድንጋጤ ተጋርጦባቸዋልይላል የተባበሩት መንግሥታት መረጃ፤ የሩስያና የዩክሬን ጦርነት የምግብ እና የነዳጅ ዋጋ መጨመር የአህጉሩን ኢኮኖሚያዊ እይታ አደጋ ላይ ጥሏል፡፡ ዕድገቱ ማገገም ሲጀምር እና ፖሊሲ አውጪዎች የኮቪድ-19 ወረርሽኝ ማህበራዊ እና ኢኮኖሚያዊ ትሩፋትን እና ሌሎች የልማት ተግዳሮቶችን መፍታት ሲጀምሩ የጦርነቱ መጀመር የኑሮ ደረጃን የሚሸረሽር እና የማክሮ ኢኮኖሚ መዛባትን የሚፈጥር ነው፡፡

የዓለም አቀፍ የምግብ ዋጋ መጨመር የአፍሪካን ኢኮኖሚ በእጅጉ እንደሚጎዳ እና መንግሥታት ጉዳቱን ማቃለል ካልቻሉ ህብረተሰቡን አለመረጋጋት ሊፈጥር ይችላል ሲል የኦክስፎርድ ኢኮኖሚክስ አፍሪካ ዘገባ አመልክቷል፡፡

ነዋሪዎች በቀን ሦስት ጊዜ መመገብ በአፍሪካ አስቸጋሪ እየሆነ መጥቷል ይላሉ፡፡ "በቀን ሦስት ጊዜ መመገብ አስቸጋሪ ሆኖል፡፡ ዜጎች እየተራቡ ነው ብሎም በደሞዝ ለሚኖር ሰው ኑሮው እጅግ ከብዷል፡፡"

በአፍሪካ ሀገራት የዋጋ ግሽበት በምግብ ላይ በእጅጉን ጨምሯል፡፡በላቁ ኢኮኖሚ ውስጥ ካሉት ሀገራት ጋር ሲነጻጸር ሰፊ የሆነ ልዩነት አለው፡፡ በላቁ ኢኮኖሚዎች ከቅርጫቱ 15 በመቶ የሚሸፍን ይሸፍናል፤ በአፍሪካ ደግሞ ይህ ቁጥር ከ25 በመቶ በላይ ሆኖል፡፡ አንዳንድ ሀገራት ኢትዮጵያ፣ዛምቢያ፣ሱዳን እና ናይጄሪያ የምግብ ግሽበቱ ከ50 በመቶ በላይ ሲኖራቸው፣ኢኮኖሚስቶቹ ዣክ ኔል እና ፔትሮ ቫን ኤክ ‹‹በኦክስፎርድ ኢኮኖሚክስ አፍሪካ›› በምርምር ማስታወሻ ላይ ጽፈዋል፡፡

በዩክሬን ያለው ጦርነት፣ እንደ ፓልም ዘይት ወደ ውጭ መላክን መከልከሉ፣ የአቅርቦት ሰንሰለት ችግር እና የአሜሪካን የስንዴ ሰብል ድርቅ መመታት የዋጋ ንረቱን አስከትሏል፡፡ ባለፈው ዓመት ከተጠበቀው 4.5 በመቶ ዕድገት በዚህ ዓመት ወደ 3.8 በመቶ እንደሚቀንስ ይጠበቃል፡፡ እንደ የቅርብ ጊዜው አህጉራዊ ኢኮኖሚ እይታ የዋጋ ግሽበት እ.ኤ.አ. በ2022 እና በ2023 በ12.2 በመቶ እና በ9.6 በመቶ በቅደም ተከተል እንደሚቀጥል ይጠበቃል፡፡ከ2008 ወዲህ ለመጀመሪያ ጊዜ የአፍሪካ አማካኝ የዋጋ ግሽበት ከፍተኛ ደረጃ ላይ ይደርሳል፡፡

በመጋቢት ወር የተባበሩት መንግሥታት የምግብናእርሻ ድርጅት (FAO ) የምግብ ዋጋ መረጃ ጠቋሚ በ13 በመቶ ጨምሯል ይላል፤ ይህም በተመዘገበው ፍጥነት በሚያዝያ ወር በትንሹ ከመቀነሱ በፊት ከፍ ያለ የምግብ ዋጋ ከነዳጅ ሂሳቦች እና ከስራ አጥነት መጨመር ጋር ተዳምሮ በአህጉሪቱ ተለዋዋጭ የፖለቲካ ምህዳር ይፈጥራል፡፡

ገብርኤል በተባበሩት መንግሥታት የምግብናእርሻ ድርጅት የአፍሪካ ምክትል ዳይሬክተር ናቸው ፡፡የምጣኔ ሀብት ድቀቱ በ54ቱም የአፍሪካ ሀገራት ላይ ጫና ማሳደሩን አልሸሸጉም፡፡

"ይሄ ጦርነት ማለትም የዩክሬን ጦርነት በምግብ ሸቀጦች ላይ ዋጋ መጨመሩ ቀጣይነት ያለው ነው ፤ወደ ሌሎችም ሀገራት እንደሚሰፋ አልጠራጠርም ይላሉ"

መንግሥታት በበጀቱ ማጠቃለያ ላይ እንኳን ምላሽ እንዲሰጡ አነሳስቷቸዋል ብለዋል ኔል እና ቫን ኤክ፡፡ ጥቂት የሚባሉ የአፍሪካ ሀገራት የሚመጣውን ችግር ከወዲሁ በማገናዘብ መፍትሄ ለመስጠት ሙከራ እያደረጉ ነው፡፡ ለአብነትም ግብፅ እና ናይጄሪያ የምግብ እና የነዳጅ ዋጋ ላይ የሚጨመረውን ገንዘብ ከእቅዳቸው ዘግይተዋል፡፡
በሌላ በኩል ሞሮኮ ፣ኬንያ እና ቤኒን ዝቅተኛ የደመወዝ ጭማሪ ማድረጋቸው አይዘነጋም፡፡ ደቡብ አፍሪካ ስራ ለሌላቸው ወርሃዊ አበል አራዝማለች እንዲሁም አጠቃላይ የነዳጅ ቀረጥ ለሁለት ወራት አቋርጣለች፡፡

እንደ ጋና እና ቱኒዚያ ያሉ የበጀት ክንፋቸው የተቆረጠ እና ጠቃሚ ድጋፍ ማድረግ ያልቻሉ ሀገራት የሕዝብ ተቃውሞ ሊገጥማቸው እንደሚችል ከወዲሁ ተገምቷል፡፡ እስከ ትላንትና ያለው መረጃ እንደሚያሳየው የጋና የዋጋ ግሽበት በሚያዝያ ወር በ18 ዓመታት ውስጥ ታይቶ የማይታወቅ ሲሆን ከፍ ማለቱን የምግብ ዋጋ ዕድገት በማስመዝገብ ከአንድ ዓመት በፊት ጋር ሲነጻጸር ወደ 26.6 በመቶ ከፍ ብሏል፡፡

ድንጋጤው ቀድሞውንም ስስ የሆነ የምጣኔ ሀብት ማመጣጠንን የበለጠ ከባድ ሊያደርገው ይችላል የሚል ስጋት አለ፡፡ በአፍሪካ ዝቅተኛ ገቢ ካላቸው ሀገሮች ውስጥ ግማሽ ያህሉ ለጭንቀት የተጋለጡ ወይም ከፍተኛ ተጋላጭ ሆነዋል ይላል መረጃው፡፡

በፍሬህይወት ታደሰ
2022-05-12