ሀገሬ ቲቪ

‘ኤምፔሳ’ የሳፋሪኮም ኢትዮጵያ የሞባይል ፋይናንስ አገልግሎት ከኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ የአገልግሎት ፍቃድ ካገኘ ከ3 ወራት በኋላ ዛሬ አገልግሎት ጀምሯል።

‘ኤምፔሳ’ የሳፋሪኮም ኢትዮጵያ የሞባይል ፋይናንስ አገልግሎት ከኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ የአገልግሎት ፍቃድ ካገኘ ከ3 ወራት በኋላ ዛሬ አገልግሎት ጀምሯል። ባለፉት 3 ወራትም አስፈላጊ የሲስተም ፍተሻዎችን እና የቴክኒክ ዝግጅቶችን ሲያደርግ መቆየቱን አስታውቋል ተቋሙ፡፡ ከባንኮች ጋር የሚያስፈልጉትን የአጋርነት ስምምነቶች በመፈራረም እንዲሁም ወኪሎችንም በመመልመል እና በማሰልጠን ወደ የሞባይል ፋይናንስ አገልግሎት መጀመሩንም ከማኀበራዊ ትስስር ገጹ ተመልክተናል። በ5 ቋንቋዎች በተዘጋጀው የኤምፔሳ መተግበሪያ ደበኞች በአገር ውስጥ ገንዘብ መላክ፣ ከአገር ውስጥና ውጪ ገንዘብ መቀበል፣ ክፍያዎችን መክፈል፣ የአየር ሰዓት መግዛት፣ ወደ ባንክ ሒሳቦቻቸው ገንዘብ ማስገባት ከባንክ ሂሳባቸው ገንዘብ ወደ ኤምፔሳ መላክ መላክ እንደሚችሉ ተነግሯል፡፡።

በሙሉጌታ በላይ
2023-08-16