የይርጋለም የግብርና ምርቶች ማቀነባበሪያ ኢንዱስትሪ ፓርክ በተጠናቀቀው በጀት ዓመት ለውጭ ገበያ ካቀረባቸው ምርቶች ከ2 ነጥብ 1 ሚሊዮን ዶላር በላይ ገቢ ማግኘቱን የሲዳማ ክልል ኢንዱስትሪ ፓርኮች ልማት ኮርፖሬሽን አስታወቀ።
ፓርኩ በ2015 በጀት ዓመት የአቮካዶ ድፍድፍ ዘይት፣ የተቀነባበረ ወተትና የተለያየ ጣዕም ያላቸው ጭማቂዎችን ለውጭ ገበያ ማቅረብ ጀምሯል።
ባለሃብቶቹ በተጠናቀቀው በጀት ዓመት 295 ቶን የአቮካዶ ድፍድፍ ዘይት በማምረት ወደ ውጭ መላካቸው ተነግሯል።
ከዚህም ከ1 ነጥብ 9 ሚሊዮን ዶላር የሚበልጥ ገቢ መገኘቱ ተወስቷል፡፡
በተጨማሪም 120 ቶን የተለያየ ጣዕም ያላቸው የፍራፍሬ ጭማቂዎችን ወደ ሱዳንና ደቡብ ሱዳን በመላክ 288 ሺህ ዶላር ገቢ ተገኝቷልም ተብሏል፡፡
ከውጭ የሚገቡ ምርቶችን በመተካት ለሀገር ውስጥ ካቀረባቸው የተለያየ ጣዕም ካላቸው የጭማቂ ምርቶች እና የተቀነባበረ ወተት 218 ሺህ ዶላር ወጪ እንዳዳነም ተነግሯል።
ፓርኩ ባለፉት አራት ዓመታት ለውጭ ገበያ ካቀረበው 1 ሺህ 300 ቶን ምርት ከ8 ነጥብ 5 ሚሊዮን ዶላር በላይ ገቢ ማስገኘቱን ከፓርኩ የተገኘው መረጃ ያመለክታል።
በብሩክታዊት አስራት
2023-12-08
