ሀገሬ ቲቪ

ሱዳን በአሁኑ ጊዜ ከ50 ሚሊዮን ዶላር በላይ የተጠቀመችበትን የኤሌክትሪክ ሃይል ክፍያ አልፈጸመችም ሲል የኢትዮጵያ ኤሌትሪክ ኃይል አስታወቀ።

ሱዳን በአሁኑ ጊዜ ከ50 ሚሊዮን ዶላር በላይ የተጠቀመችበትን የኤሌክትሪክ ሃይል ክፍያ አልፈጸመችም ሲል የኢትዮጵያ ኤሌትሪክ ኃይል አስታወቀ።

በሱዳን ያለው ግጭት ከመጀመሩ አስቀድሞ ክፍያዋን በአግባቡ የፈፀመች መሆኑንና ከተፈጠረው ግጭት በኃላ ግን መክፈል ማቆሟን አገልግሎቱ አስታውቋል፡፡

ይህም በውጭ ጉዳይ ሚኒስቴርና በኢትዮጵያ በሱዳን አምባሳደር በኩል ያሉ ክፍተቶችን እንዲፈቱ እየተሰራ መሆኑ ተነግሯል፡፡

በ2015 በጀት ዓመት ኢትዮጵያ ለጎረቤት አገራት ከምታቀርበው የኤሌክትሪክ ኃይል ሽያጭ ከ102 ሚሊዮን ዶላር በላይ ማግኘቷንም አገልግሎቱ አስታውቋል፡፡

ኢትዮጵያ ይህን ገቢ ያገኘችው ለጅቡቲ፣ ለሱዳንና ለኬንያ የኤሌክትሪክ ኃይልን ከሸጠችው ላይ ነው።

የተገኘው ገቢ በ2014 በጀት ዓመት ጋር ሲነጻጸርም ከጅቡቲ የተገኘው ገቢ አራት በመቶ ጭማሪ ቢያሳይም ከሱዳን የተገኘው ገቢ ግን 34 በመቶ ቅናሽ ማሳየቱን የኢትዮጵያ ፕረስ ድርጅት ዘግቧል።

በናርዶስ ታምራት
2023-08-17