ሀገሬ ቲቪ

የኢትዮጵያ ልማት ባንክ በ2016 በጀት ዓመት 51 ቢሊዮን ብር ብድር ለመስጠት መዘጋጀቱን አስታወቀ። የባንኩ አጠቃላይ የብድር መጠኑ 75 ቢሊዮን ብር በላይ መድረሱም ተመላክቷል።

የኢትዮጵያ ልማት ባንክ በ2016 በጀት ዓመት 51 ቢሊዮን ብር ብድር ለመስጠት መዘጋጀቱን አስታወቀ።

የባንኩ አጠቃላይ የብድር መጠኑ 75 ቢሊዮን ብር በላይ መድረሱም ተመላክቷል።

ባንኩ በ2015 በጀት ዓመት 6 ነጥብ 4 ቢሊዮን ብር ማትረፉን እና የባንኩ አጠቃላይ ካፒታልም በ2011 በጀት ዓመት ከነበረበት 2 ነጥብ 6 ቢሊዮን ብር፤ በ2015 በጀት ዓመት ወደ 38 ቢሊዮን ብር ከፍ ማለቱ ይታወሳል፡፡

በቀጣይ ጊዜያትም የውጭ ምንዛሪ ለሚያስገኙ ምርቶች እና ተኪ ምርቶች ላይ ትኩረት አድርጎ ፋይናንስ እንደሚያደርግ አስታውቋል።

ከዚህ ቀደም በዋስትና ምክንያት የብድር አቅርቦት ችግር እንዳያጋጥማቸው ፕሮጀክቶችን በማስያዣነት ተጠቅሞ ብድር ሲሰጥ መቆየቱንና ይህም ባለሀብቶች በዋስትና ችግር ከኢንቨስትመንት እንዳይወጡ ማድረግ ማስቻሉ ተነግሯል፡፡

በ2016 የተያዘው በጀት ከወለድ ነጻ የፋይናንስ አቅርቦትን የሚያካትት መሆኑ ተጠቁሟል፡፡

በአብርሃም በለጠ
2023-08-17