በኢትዮጵያ በ10 ዓመት ውስጥ በኤሌክትሪክ የሚሰሩ 48 ሺህ አውቶብሶችን ወደ ስራ ለማስገባት እየተሰራ መሆኑን የትራንስፖርት እና ሎጂስቲክስ ሚኒስቴር አስታወቀ፡፡
ሚኒስቴሩ ከዚህ በተጨማሪ 148 ሺህ አውቶሞቢሎችንም በአስር ዓመት ውስጥ ወደስራ ለማስገባት እየሰራ መሆኑንም ተናግሯል፡፡
በኤሌክትሪክ ኃይል የሚሰሩ ተሽከርካሪዎችን ለማስፋፋት በትኩረት እየተሰራ እንደሆነም ገልጿል፡፡
የኤሌክትሪክ ተሽከርካሪዎችን በማስፋፋት የትራንስፖርት ዘርፉን ከነዳጅ ጥገኝነት ለማላቀቅ እየተሰራ ሲሆን ኢትዮጵያ ለነዳጅ ግዢ የምታውለውን የውጪ ምንዛሪን ያስቀራልም ተብሏል፡፡
በኤሌክትሪክ ኃይል የሚሰሩ ተሽከርካሪዎች እንዲስፋፉ መንግሥት እያደረገ ያለው የቀረጥ ማበረታቻ ዘርፉን በከፍተኛ ሁኔታ እንደሚያግዝ ተጠቁሟል፡፡
በወንድማገኝ አበበ
2023-08-17
