ሀገሬ ቲቪ

በ2016 ዓ.ም ከቡና የወጪ ንግድ 1.7 ቢሊዮን ብር ለማግኘ መታቀዱ ተገለፀ

የኢትዮጵያ ቡናና ሻይ ባለሥልጣን በ2016 በጀት ዓመት በቡና የወጪ ንግድ 1 ነጥብ 7 ቢሊዮን ዶላር ለማግኘት ማቀዱን አስታወቀ።

ባለሥልጣኑ በቡና ዘርፉ ላይ የሚስተዋሉ ችግሮችን በመቅረፍ 350 ቶን ቡና ለውጭ ገበያ ለማቅረብ ማቀዱንም ገልጿል።

ከሀገሬ ቴሌቪዥን ጋር ቆይታ ያደረጉት የባለስልጣኑ ምክትል ሥራ አስፈፃሚ አዳዲስ የገበያ አማራጮችን በማስፋት የኢትዮጵያን ቡና ለአለም ገበያ በሰፊው ለማድረስ እንደሚሰራም ተናግረዋል።

የኢትዮጵያን ቡና እሴት ጨምሮ ለገበያ ለማቅረብም ስራዎች እየተሰሩ መሆኑን ጠቁመዋል።

በማህሌት አማረ
2023-08-25