ሀገሬ ቲቪ

የአማራ ክልል ምክር ቤት 6ኛ ዙር 2ኛ ዓመት የሥራ ዘመን 1ኛ አስቸኳይ ጉባዔ በባህርዳር ከተማ ማካሄድ ጀምሯል።

የአማራ ክልል ምክር ቤት 6ኛ ዙር 2ኛ ዓመት የሥራ ዘመን 1ኛ አስቸኳይ ጉባዔ በባህርዳር ከተማ ማካሄድ ጀምሯል።

ምክር ቤቱ ለአንድ ቀን በሚያካሄደው አስቸኳይ ጉባዔው በክልሉ በወቅታዊ ሰላምና ደህንነት ጉዳይ አተኩሮ እንደሚወያይም ተመላክቷል።

በዚህ አጀንዳ ዙሪያ በጥልቀት ከተወያየ በኋላም ችግሮች በዘላቂነት በሚፈቱበት መንገድ የቀጣይ አቅጣጫ ያስቀምጣል ተብሎ ይጠበቃል።

ምክር ቤቱ ልዩ ልዩ ሹመቶችን በመስጠት ለአንድ ቀን የጠራውን አስቸኳይ ጉባዔ እንደሚያጠናቅቅ ኢዜአ ዘግቧል፡፡

በአብርሃም በለጠ
2023-08-25