ሀገሬ ቲቪ

የሰሜኑ ጦርነት በሰላም ስምምነት ከተቋጨ በኋላ በርካታ ሴቶች እና ልጃገረዶች ላይ ፆታዊ ጥቃቶች ደርሰዋል ተባለ፡፡

የሰሜኑ ጦርነት በሰላም ስምምነት ከተቋጨ በኋላ በርካታ ሴቶች እና ልጃገረዶች ላይ ፆታዊ ጥቃቶች ደርሰዋል ተባለ፡፡

አሶሼትድ ፕረስ ባወጣው ዘገባ በሕክምና መዝገቦች ላይ በተደረገ አዲስ ጥናት በኢትዮጵያ ትግራይ ክልል ግጭቱ ከተፈታ በኋላ ቢያንስ 128 ሴቶች ፆታዊ ጥቃት ተፈፅሞባቸዋል ብሏል።

አብዛኛው ፆታዊ ጥቃቶች የተፈጸሙት በተዋጊዎች እንደ ሆነ ጥናቱ አመላክቷል።

አብዛኛዎቹ የጤና ተቋማት በጦርነት የወደሙ ሲሆን በዚህም በርካታ ሴቶችና ልጃገረዶች ለወራት ያለህክምና ቆይተዋል።

በወንድማገኝ አበበ
2023-08-25