ሀገሬ ቲቪ

የአሜሪካ የአፍሪካ ቀንድ ልዩ መልዕክተኛ ማይክ ሀመር ወደ ኢትዮጵያ እና ኬንያ ሊመጡ ነው ተባለ።

የአሜሪካ የአፍሪካ ቀንድ ልዩ መልዕክተኛ ማይክ ሀመር ወደ ኢትዮጵያ እና ኬንያ ሊመጡ ነው ተባለ።

ልዩ መልዕክተኛው በሀገራቱ የአስር ቀን ቆይታ እንደሚኖራቸውም ተገልጿል።

ማይክ ሀመር በቆይታቸው ከሀገራቱ ከፍተኛ ባለሥልጣናት፣ ከአፍሪካ ህብረት፣ የመንግሥታት ማህበሮች እና ዓለም አቀፍ አጋሮች ጋር እንደሚመክሩ የዩናይትድ ስቴትስ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር በገጹ አስታውቋል።

ልዩ መልዕክተኛው በሱዳን እና በኢትዮጵያ ያሉት ግጭቶች ስለሚቆሙባቸው ሁኔታዎች እንደሚመክሩም ተመላክቷል።

በአብርሃም በለጠ
2023-08-29