ሀገሬ ቲቪ

አሜሪካ ዜጎቿን ተጨማሪ የኮቪድ ክትባት ልትከትብ ነው፡፡

አሜሪካ ዜጎቿን ተጨማሪ የኮቪድ ክትባት ልትከትብ ነው፡፡

ባይደን ለአዲሱ የኮቪድ ክትባት ግዢ የሚሆን ተጨማሪ ገንዘብ እንዲሰጣቸው አሜሪካ ኮንግረስን ለመጠየቅ ማቀዳቸውን አስታወቁ።

ፕሬዚዳንቱ ለአዲሱ ክትባት ተጨማሪ የገንዘብ ድጋፍ ጥያቄን ለኮንግረሱ ለማቅረብ መፈረማቸውን ተናግረዋል።

ሁሉም ሰው አዲሱን ክትባት እንዲወስድም ማሳሰቢያን ሰጥተዋል።

የአሜሪካ የበሽታ መቆጣጠሪያ እና መከላከያ ተቋም (ሲዲሲ) በኮቪድ የሚያዙ ሰዎች እና የሚሞቱ ሰዎች ቁጥር እያሻቀበ እንደሚገኝ አስታውቋል።

ከዚህ ቀደም የፕሬዝዳንቱ አስተዳደር ቫይረሱን ለመከላከል 9.25 ቢሊዮን ዶላር የገንዘብ ድጋፍ መጠየቁ እና ኮንግረሱ አልቀበልም ማለቱ ይታወሳል።

በብሩክታዊት አስራት
2023-08-29