በኢትዮጵያ መንግሥት አንድ ሚሊዮን የዲጂታል መታወቂያ ካርዶችን ለማምረት የሚያስችል የባዮሜዲካል መረጃዎችን ለመሰብሰብ የማድራስ ሴኪዩሪቲ ፕሪንተርስን ከተባለ ተቋም ጋር ውል ማሰሩ ተጠቆመ፡፡
የህንድ መሰረት ያለው ተቋሙ 10 ተጫራቾችን በመብለጥ ለኢትዮጵያ የዲጂታል መታወቂያዎችን እንዲያመርት በ300,000 ዶላር ጨረታን በማሸነፍ መመረጡን አፍሪካ ኢንተለጀንስ ዘግቧል።
ስምምነቱ ዲጂታል መታወቂያን የሚያሰሩ ዜጎችን መረጃ ለማረጋገጥ የሚያስችሉ መረጃዎችን ለመሰብሰብ መሆኑ ተነግሯል፡፡
በኢትዮጵያ ለብሄራዊ ዲጂታል መታወቂያ እስካሁን ከ1.4 ሚሊዮን በላይ ዜጎች መመዝገባቸው ተነግሯል፡፡
በብሩክታዊት አስራት
2023-09-01
