የኢኳዶሩ ፕሬዝዳንት ዳንኤል ኖቦኣ፤ በሀገሪቱ የሚገኙ እጽ አዘዋዋሪዎችን ለማጥፋት በሚል ጦርነት አወጁ።
ፕሬዝዳንቱ ጦርነቱን ያወጁት እጽ አዘዋዋሪ ቡድኖቹ ለሶስት ቀናት የቆየና በመሳሪያ የተደገፈ ግጭት ከሀገሪቱ ብሔራዊ ጦር ጋር ካከናወኑ በኋላ ነዉ ተብሏል።
ፕሬዝዳንቱ ቡድኖቹ የሽብር ተግባር ነዉ የፈጸሙት ያሉ ሲሆን፤ በጦርነት ላይ ነን ለእነዚህ አሸባሪዎች እጅ አንሰጥም ማለታቸዉን አናዶሉ ዘግቧል።
እጽ አዘዋዋሪ ቡድኖቹ ለሶስት ቀናት በከፈቱት ተኩስ ሰዎች መሞታቸዉንና ከመቶ በላይ ሰዎችን አግተዉ መዉሰዳቸዉ ተነግሯል።
በማህሌት አማረ
2024-01-11
