ትውልደ ኢትዮጵያዊቷ እግር ኳስ ተጫዋች ናኦሚ ግርማ የ2023 የአሜሪካ የዓመቱ ምርጥ ሴት ተጫዋች ተብላ ተመረጠች፡፡
ይህም ከ39 ዓመት በኋላ በታሪክ የመጀመሪያዋ ተከላካይ ተጫዋች አስብሏታል፡፡
ተጫዋቿ ለአሜሪካው ሳን ዲያጎ ዌቭ ክለብ የምትጫወት ሲሆን በሽልማቱ ታሪክም የመጀመሪያዋ የተከላካይ ተጫዋች ተብላለች፡፡
የ 23 ዓመቷ ናኦሚ ግርማ የዓመቱ ምርጥ ወጣት ተጫዋች እና የዓመቱ ምርጥ ተጫዋች ሽልማትን አንድ ላይ በማሸነፍ ስድስተኛዋ ናት።
ናኦሚ ግርማ ከሽልማቱ በኋላ ስትናገርም "ይህንን ሽልማት ያሸነፈች የመጀመሪያዋ ተከላካይ እና ሁለተኛዋ ጥቁር ተጫዋች በመሆኔ ክብር ይሰማኛል" ስትል ተደምጣለች።
ተጫዋቿ በቅርቡ ለሁለት ተከታታይ ዓመታት የሊጉ ምርጥ ተከላካይ መባሏ እንዲሁም የዓመቱ ምርጥ ስብስብ ውስጥ መካተቷ ይታወሳል።
በይገደብ ዓባይ
2024-01-12
