ሀገሬ ቲቪ

የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል በ2016 የመጀመሪያው ግማሽ ዓመት አገልግሎት የማይሰጡ የተለያዩ ንብረቶችን በማስገድ 66 ነጥብ 2 ሚሊዮን ብር ገቢ ማግኘቱን አስታወቀ፡፡

የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል በ2016 የመጀመሪያው ግማሽ ዓመት አገልግሎት የማይሰጡ የተለያዩ ንብረቶችን በማስገድ 66 ነጥብ 2 ሚሊዮን ብር ገቢ ማግኘቱን አስታወቀ፡፡

ገቢው አገልግሎት የማይሰጡ ተሸከርካሪዎችን፣ ቁርጥራጭ ብረቶችን፣ አሉሙኒየምና መዳቦችን በማስወገድ የተገኘ ነው ተብሏል፡፡

የተገኘው ገቢ ካለፈው ዓመት ተመሳሳይ ወቅት ጋር ሲነፃፀር የ14 ነጥብ 7 ሚሊዮን ብር ብልጫ እንዳለው ተገልጿል፡፡

ተቋሙ አገልግሎት የማይሰጡ ንብረቶችን በማስወገድ የሚያገኘው ገቢ ከጊዜ ወደ ጊዜ እያደገ መምጣቱን ያስታወቀ ሲሆን ከንብረት ርክክብ፣ ከጨረታና ከባለቤትነት ጋር ማረጋገጫ ሰነድ ጋር የተያያዙ ችግሮች በሥራው ላይ ጫና እያሳደሩ መሆኑ ተጠቅሷል።

በበጀት ዓመቱ መጨረሻም 150 ሚሊዮን ብር ገቢ ለመሰብሰብ መታቀዱን ከኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል ማህበራዊ ትስስር ገፅ ተመልክተናል።

በብሩክታዊት አሥራት
2024-01-12