ሀገሬ ቲቪ

የኢትዮጵያ ቅርስ ባለስልጣን ለትግራይ ክልል ቅርስና ቱሪዝም መዳረሻዎች ጥገና የሚውል 5 ሚሊዮን ብር ድጋፍ ማድረጉ ተነገረ።

የኢትዮጵያ ቅርስ ባለስልጣን ለትግራይ ክልል ቅርስና ቱሪዝም መዳረሻዎች ጥገና የሚውል 5 ሚሊዮን ብር ድጋፍ ማድረጉ ተነገረ።

በትግራይ ክልል የቱሪዝም ኢንዱስትሪውን ለማነቃቃትና የጎብኚዎችን ቁጥር ለማሳደግ የቅርሶችና የቱሪዝም መዳረሻዎች ጥገና እየተከናወነ ይገኛል።

የቱሪዝም ሚኒስቴር ከቅርስ ባለስልጣን ጋር በመተባበር በአክሱም፣ ዓድዋ፣ ዓዲግራት ተምቤን፣ ገርዓልታ፣ ውቅሮና አልነጃሽ አካባቢዎች የሚገኙና ጥገና የሚያስፈልጋቸው 21 ቅርሶችና መዳረሻዎች በአስቸኳይ የጥገናና ማልማት ስራ እየተሰራ መሆኑ ተመላክቷል።

የቱሪዝም እንቅስቃሴውንም ለማነቃቃት ባለስልጣኑ ከክልሉ ጊዜያዊ አስተዳደር ባህልና ቱሪዝም ቢሮ ጋር በመተባበር ሃላፊነቱን እየተወጣ እንደሚገኝም ኢዜአ ዘግቧል።

በክልሉ በተለያዩ ምክንያቶች የቱሪስት ፈሰት እንቅስቃሴ ተቀዛቅዞ መቆየቱ ይታወሳል።

በብሩክታዊት አሥራት
2024-01-15