የኦሮሞ ፌዴራልዊ ኮንግረስ ኦፌኮ ከረዥም በኃላ በሰጠው መግለጫ ሁለት ዋና ዋና ጉዳዮችን ተመልክቻለሁ ብሎል፡፡የፖለቲካ ዉጥረት፣ ኢኮኖሚ፣ የእርስ በእርስ ጦርነት ማየል 2ተኛው ደግሞ ሀገራዊ ውይይት ይደረግ በሚለዉ ላይ ማብራሪያ ሰጥቶል፡፡
በመግለጫዉ ከፍተኛ የሕዝብ ቁጥር ባለው በኦሮሚያ ክልል ከፍተኛ ጦርነት እየተካሄደ ነዉ ሲል ሕግ አስከባሪውን መንግሥትን ጠይቋል፡፡
የኦፌኮ የሕዝብ ግንኙነት ኀላፊ የሆኑት አቶ ሱልጣን ቃሲም እንደተናገሩት ከሆነ “ባለፋት ጥቂት ወራት ብቻ ከ297 በላይ ንፁሃን በመንግሥት ታጣቂዎች ሲገደሉ በርካታ ቤቶች ተቃጥለዋል በጦርነቱ 500ሺሕ በላይ ዜጎች ተፈናቅለዋል፡፡”
በተጨማሪም “በመቶዎች የሚቆጠሩ ትምህርት ቤቶች ተዘግተዋል፣ ቤቶች ተቃጥለዋል ሆስፒታሎች እና ጤና ጣቢያዎች አገልግሎት አልባ ሆነዋል ሰዎች ያለ ፍርድ ቤት ትእዛዝ በግፍ እየታሰሩ ነው፤ ማሰቃየትና ያለ ፍርድም ይገደላሉ” ሲሉ በአጽንዖት ተናግረዋል፡፡
በተለያዩ የሀገሪቱ ክፍሎች በተለይም በሰሜን ኢትዮጵያ የእርስበርስ ጦርነት በርካቶች ሞቶች፣ መፈናቀሎች እና ንብረት ዉድመቶች ተከስቷል፡፡
በሀገሪቷ የሃይማኖት እና የዘር ግጭቶች፣የዋጋ ንረት፣ረሃብ፣የኢኮኖሚ ማዕቀብ እና በዘር የታጠቁ አካላት ጉዳይ አስቸጋሪ ናቸው ብለዋል፡፡
በኦሮሚያና በተለያዩ የሀገሪቷ ክፍሎች በመንግሥት ታጣቂዎች ጭምር በሰላማዊ ዜጎች ላይ የተፈፀሙ ያሉ ግድያዎች በዓለም አቀፍ ገለልተኛ አካላት በመጣራት ለፍርድ እንዲቀርቡ ተጠይቋል፡፡
ሊቀመንበሩ መረራ ጉዲና (ፕ/ር) ሲናገሩ “ሀገራችንን ለመታደግ እዉነተኛ ሀገራዊ ውይይት ብቸኛ መፍትሄ ነዉ ይላሉ፡፡ በተለይም መንግሥት የሚያደራጃቸው የብሄራዊ ውይይት አካላት ባለው ነባራዊ ሁኔታ ላይ ችግር የሚፈጥር እንጂ ችግር ፈቺ አይደለም ስለዚህ ይታሰብበት፡፡” ብለዋል
የኦፌኮና የኦነግ አመራር አባላት ጨምሮ ሁሉም የፖለቲካ እስረኞች እንዲፈቱም ተጠይቋል፡፡ጦርነትቱ በአፋጣኝ እንዲቆም እና ወደ ድርድር ይገባ ሲል ፖርቲው ጠይቋል፡፡
በፍሬህይወት ታደሰ
2022-05-13
