ሀገሬ ቲቪ

የጋራ መኖሪያ ቤቶች ጥራታቸው ተጠብቆ ባለመገንባታቸው ዕድለኞች ለከፍተኛ ወጪ መዳረጋቸውን አንድ ጥናት አመላከተ።

የጋራ መኖሪያ ቤቶች ጥራታቸው ተጠብቆ ባለመገንባታቸው ዕድለኞች ለከፍተኛ ወጪ መዳረጋቸውን አንድ ጥናት አመላከተ።

ጥናቱን የከወኑት የአፍሪካ ከተሞች የምርምር ጥምረት (ACRC) እና ‹‹ፎረም ፎር ሶሻል ስተዲስ›› (FSS) ናቸው።

መንግሥት 40/60 ወይም የ20/80 የጋራ መኖሪያ ቤቶችን በዕጣ ለደረሳቸው ሲያቀርብ ጥራታቸውን በጠበቀ መንገድ ስለማይገነቡ ዕድለኞች መልሰው አፍርሶ ለመሥራት እንደሚገደዱና ከፍተኛ ወጪ እንደሚያወጡ የአፍሪካ ከተሞች የምርምር ጥምረት ተመራማሪና የምርምር ሥርፀት አስተባባሪ ኢዛና ዓምደወርቅ (ዶ/ር) ለሪፖርተር ገልፀዋል።

የጋራ መኖሪያ ቤት የደረሳቸው ዕድለኞች ለኤሌክትሪክ ኃይል ዝርጋታ፣ የሲራሚክ ንጣፍ፣ ለመፀዳጃ ቤት መስመር፣ ግድግዳ እንደገና ለመሥራትና ሌሎች የጎደሉ ነገሮች ለማሟላት ለከፍተኛ ወጪ እንደሚዳረጉም ጥናቱ ያሳያል፡፡

እነዚህ ጉዳዮች ከፍተኛ ትኩረት የሚፈልጉ በመሆናቸው፣ መንግሥት ለጋራ መኖሪያ ቤቶች ግንባታ ከግብዓት ጀምሮ እስከ ባለሙያ ድረስ ጥራታቸውን በመጠበቅ ማቅረብ እንደሚኖርበት መግለፃቸውን ሪፖርተር አስነብቧል፡፡

በብሩክታዊት አሥራት
2024-01-15