የኢትዮጵያ ፓስፖርት ዓለም አቀፍ ተቀባይነቱ ከጊዜ ወደ ጊዜ እየቀነሰ ነው ተባለ፡፡
የኢትዮጵያ ፓስፖርት በሐምሌ ወር ከነበረበት የዓለማቀፍ ተቀባይነት ደረጃ በአራት ደረጃ ማሽቆልቆሉን የሄንሊይ ፓስፖርቶች ደረጃ አውጭ ሪፖርት አስታወቋል፡፡
የኢትዮጵያ ፓስፖርት 93ኛ ደረጃ ላይ እንደሚገኛ ሪፖርቱ ላይ ተመላክቷል፡፡
ለሀገሪቱ ፓስፖርት በዓለማቀፍ ደረጃ መቀነስ የግጭቶች መበራከት በምክንያትነት ተጠቅሷል።
የኬንያ ፓስፖርት 67ኛ ደረጃ ላይ ሲኾን፣ የኡጋንዳ 73ኛ ደረጃ ላይ ይገኛል። የሱዳን ፓስፖርት ደረጃ ቀደም ሲል ከነበረበት በሁለት ደረጃዎች ቀንሶ፣ አሁን 95ኛ ደረጃ ተሰጥቶታል።
ኬንያዊያን ያለ ቪዛ መጓዝ የሚችሉባቸው አገራት ብዛት 76 ሲሆኑ፣ ኢትዮጵያዊያን ያለ ቪዛ የሚጓዙባቸው አገራት 47 ብቻ እንደሆኑ ሪፖርቱ ላይ ተጠቅሷል፡፡
በናርዶስ ታምራት
2024-01-15
