ሀገሬ ቲቪ

የትግራይ ክልል አዲስ ያወጣው የፖሊሶች መመልመያ ደንብ ቅሬታ ቀረበበት፡፡

የትግራይ ክልል አዲስ ያወጣው የፖሊሶች መመልመያ ደንብ ቅሬታ ቀረበበት፡፡

የትግራይ ጊዜያዊ አስተዳደር ካቢኔ ባለፈው ህዳር ያወጣው አዲስ ደንብ የዜጎችን መብት ይገድባል የሚል አቤቱታ በሕገ መንግሥት ትርጉም አጣሪ ጉባዔ እንደቀረበበት ተሰምቷል።

የሕገመንግሥት ትርጉም አቤቱታውን ያቀረበው "ቅድሚያ ለሰብዓዊ መብቶች" ሲቪል ማኅበር እንደኾነ ሪፖርተር ዘግቧል።

ማኅበሩ አቤቱታ ያቀረበበት አንዱ የደንቡ ድንጋጌ፣ በመንግሥትና በግል ሠራተኞች ውዝፍ ደመወዝ ዙሪያ በፍርድ ቤት የተመሠረቱ ክሶች ለጊዜው ታግደው እንዲቆዩ በሚደነግገው አንቀጽ እንደኾነ ዘገባው አመልክቷል።

አዲሱ የክልሉ ፖሊስ ማቋቋሚያ አዋጅ በነባር ፖሊሶች ፋንታ የትግራይ ተዋጊዎች ብቻ በፖሊስነት እንዲመለመሉ የሚጠይቀው የደንቡ ክፍልም፣ የሕገመንግሥት ትርጉም አቤቱታ ቀርቦበታል ተብሏል።

በናርዶስ ታምራት
2024-01-15