ከቆዳና ሌጦ ዘርፍ ሊገኝ ከታቀደው ገንዘብ 10.2 ሚሊዮን ዶላር ሳይገኝ መቅረቱ ተነገረ።
ኢንዱስትሪ ሚኒስቴር በስድስት ወራት ውስጥ ከቆዳና ሌጦ ዘርፍ 25 ሚሊዮን ዶላር ለማግኘት ቢያቅድም ማግኘት የተቻለው 14.8 ሚሊዮን ዶላር ብቻ መሆኑን አስታውቋል፡፡
ይህም ማለት ከተያዘው ዕቅድ 10.2 ሚሊዮን ዶላር ገቢ ሳይገኝ መቅረቱን ሚኒስቴር መሥሪያ ቤቱ ለሀገሬ ቴቪ ተናግሯል።
ለቆዳ ኢንዱስትሪዎች እየቀረበ ከሚገኘው ጥሬ ቆዳ ውስጥ 50 በመቶ ያህሉ የበዛ የጥራት ችግር የሚታይበት ነው ተብሏል።
ይህን መሰል ተያያዥ ተግዳሮቶች ለገቢው ማሽቆልቆል ምክንያት ተደርገው ተጠቅሰዋል።
በናርዶስ ታምራት
2024-01-16
