ሀገሬ ቲቪ

ብሔራዊ ቴአትር እና ስፖርት አካዳሚ በብልሹ አሠራር ተተቹ።

ብሔራዊ ቴአትር እና ስፖርት አካዳሚ በብልሹ አሠራር ተተቹ።

በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የጤና፣ ማህበራዊ ልማት እና ባህልና ስፖርት ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ የባህልና ስፖርት ሚኒስቴር የ2016 በጀት ዓመት የአምስት ወራት ዕቅድ አፈጻጸም ገምግሟል፡፡

በግምገማው ወቅት በኢትዮጵያ ብሄራዊ ቴአትር እና በስፓርት አካዳሚ ላይ የሚሰሩ የማሻሻያ ሥራዎች ላይ ውስብስብ ችግሮች መኖራቸውን የቋሚ ኮሚቴው ሰብሳቢ ወ/ሮ ወርቅሰሙ ማሞ ጠቁመዋል፡፡

በተለይም በብሄራዊ ቴአትር የአመራር ድክመት መኖሩ ተነስቷል፡፡

ሚኒስቴር መሥሪያ ቤቱ እነዚህ በተቋማቱ ላይ የሚታዩ ችግሮችን በሁለት ወር ጊዜ ውስጥ ማስተካከያ እንዲያደርግ ወ/ሮ ወርቅሰሙ አሳስበዋል፡፡

በይስሃቅ አበበ
2024-01-16