የድሬዳዋ ሸንሌ የመንገድ ግንባታ ፕሮጀክት መጓተቱ ተገለፀ።
በ2012 ዓ.ም የተጀመረው የድሬዳዋ ሸንሌ የመንገድ ግንባታ ፕሮጀክት በታቀደለት የጊዜ ገደብ መጠናቀቅ እንዳልቻለ ተገለፀ።
የመንገድ ግንባታው 53 በመቶ ብቻ መጠናቀቁን የከተማ መሰረተ ልማት እና ትራንስፖርት ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ በቦታው ተገኝቶ ባደረገው ቅኝት መመልከቱን ገልጿል።
ከ750 ሚሊዮን ብር በላይ የካሳ ክፍያ ተከፍሎ ያልተነሱ የመብራት መሰረተ ልማቶች መኖር፣ የነዳጅ እና የሲሚንቶ አቅርቦት ችግር መኖር ለፕሮጀክቱ መጓተት ምክንያት መሆኑ ተገልጿል።
የመንገድ ግንባታው በ2017 ዓ.ም እንደሚጠናቀቅ የፕሮጀክቱ ተቆጣጣሪ መሃንዲስ መናገሩን የተወካዮች ምክር ቤት በማህበራዊ ትስስር ገፁ አስፍሯል።
በሙሉጌታ በላይ
2024-01-16
