ሀገሬ ቲቪ

ዶናልድ ትራምፕ በአንድ የአሜሪካ ግዛት ዉስጥ የተደረገዉን ምርጫ አሸነፉ።

ዶናልድ ትራምፕ በአንድ የአሜሪካ ግዛት ዉስጥ የተደረገዉን ምርጫ አሸነፉ።

የቀድሞዉ የአሜሪካ ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ፤ በአሜሪካዋ ሎዋ ግዛት በሪፐብሊካኖች መካከል የተደረገዉን ምርጫ በከፍተኛ የበላይነት ማሸነፋቸዉ ታዉቋል።

በግዛቷ የሚገኙ 19 የሪፐብሊካን ኮንግረስ ተወካዮች በሰጡት ድምፅ 51 ከመቶ የሚሆነዉን በማግኘት የቀድሞዉ ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ ማሸነፋቸዉ ታዉቋል።

በተያዘዉ ዓመት ለሚደረገዉ የአሜሪካ ፕሬዝዳንታዊ ምርጫ እንደሚወዳደሩ የሚጠበቁት ትራምፕ በተለያዩ ግዛቶች ከምርጫዉ ጋር በተያያዘ እንቅስቃሴ መጀመራቸዉን አር.ቲ ዘግቧል።

በበላይሁን ፍስሐ
2024-01-16