ቻይና ምንጊዜም ከፍትህ እና ሃቅ ጎን ነው የምቆመው ስትል ተናገረች።
ሀገሪቱ ይህን ያለችው እስራዔል በጋዛ በምታደርገው ጥቃት ሞት እና የአካል ጉዳት የሚደርስባቸውን ንጹኃን ዜጎች አስመልክቶ ባስተላለፈችው መልዕክት ነው።
ቻይና፤ የፍልስጤማውያን ሕይወት ግድ ስለሚላት ጦርነቱ ስለሚቆምበት ብልሃት ከአረብ ሀገራት ጋር ለመምከር ዝግጁ መኾኗን ግብፅ የገቡት የቻይና የውጪ ጉዳይ ሚኒስትር ዋንጌይ መናገራቸውን ሲጂቲ ኤን ዘግቧል።
በሙሉጌታ በላይ
2024-01-16
