ሀገሬ ቲቪ

ፖርቹጋላዊው አንጋፋ አሰልጣኝ ጆዜ ሞሪንሆ 2 ዓመት ተኩል ካሰለጠኑበት ሮማ ተሰናብተዋል፡፡

ፖርቹጋላዊው አንጋፋ አሰልጣኝ ጆዜ ሞሪንሆ 2 ዓመት ተኩል ካሰለጠኑበት ሮማ ተሰናብተዋል፡፡

ከግንቦት 2021 ጀምሮ የጣሊያኑን ሮማ ክለብ ሲያሰለጥኑ የነበሩት ጆዜ ሞሪንሆ በዛሬው ዕለት ከኃላፊነታቸው መሰናበታቸው ይፋ ሆኗል፡፡

የቀድሞው የሮማ ኮከብ ዳንኤሌ ዴሮሲ ቀጣዩ የክለቡ አሰልጣኝ ሊሆን እንደሚችል እየተዘገበ ይገኛል፡፡

በሮም ቆይታቸው 2022 ላይ ፋዬኖርድን በመርታት የአውሮፓ ኮንፌደሬሽንስ ካፕ ዋንጫ ማሳካት ችለው ነበር፡፡

በዓመቱም ቡዳፔስት ላይ ለተደረገው ዩሮፓ ሊግ ፍፃሜ መድረስ ቢችሉም በሴቪያ ተረተዋል፡፡

የሮማ ባለቤት ዳን እና ራየን ፍሬድኪን በመግለጫቸው ሞሪንሆን ስለስራቸው ሲያመሰግኑ፤ የነበራቸውን ቆይታ ሁልጊዜም እንደሚያስታውሱት ገልጸዋል፡፡

ሮማ በሴሪ አ በ29 ነጥቦች 9ኛ ደረጃ ላይ ሲገኝ ካደረጋቸው 7 የመጨረሻ ጨዋታዎች በ4ቱ ተሸንፋል፡፡

በይገደብ ዓባይ
2024-01-16