ሀገሬ ቲቪ

ኮትዲቯር ባዘጋጀችው 34ኛው የአፍሪካ ዋንጫ ወደ ጥሎ ማለፍ ያለፉ ሀገራት የቀጣይ ጥሎ ማለፍ ጨዋታዎች ተጋጣሚዎቻቸውን አውቀዋል።

ኮትዲቯር ባዘጋጀችው 34ኛው የአፍሪካ ዋንጫ ወደ ጥሎ ማለፍ ያለፉ ሀገራት የቀጣይ ጥሎ ማለፍ ጨዋታዎች ተጋጣሚዎቻቸውን አውቀዋል። ጥሎ ማለፉን የተቀላቀሉ ሀገራት አንጎላ፣ ናሚቢያ፣ ናይጄሪያ፣ ካሜሩን፣ ኢኳቶሪያል ጊኒ፣ ጊኒ፣ ግብፅና ዲሞክራቲክ ኮንጎ ናቸው። ⚽ ቅዳሜ ጥር 18 ቀን 2016 ምሽት 2 ሰዓት አንጎላ ከናሚቢያ እንዲሁም ምሽት አምስት ሰዓት ናይጄሪያ ከካሜሩን፤ ⚽ እሁድ ጥር 19 ቀን 2016 ምሽት 2 ሰዓት ኢኳቶሪያል ጊኒ ከጊኒ እንዲሁም ምሽት 5 ሰዓት ግብጽ ከዴሞክራቲክ ኮንጎ፤ ⚽ ሰኞ ጥር 20 ቀን 2016 ምሽት 2 ሰዓት ኬፕ ቨርዴ ከሞሪታኒያ እንዲሁም ምሽት 5 ሰዓት ሴኔጋል ከ ኮትዲቯር፤ ⚽ ማክሰኞ ጥር 21 ቀን 2016 ምሽት 2 ሰዓት ማሊ ከቡርኪናፋሶ እንዲሁም ምሽት 5 ሰዓት ሞሮኮ ከደቡብ አፍሪካ ይገናኛሉ። የአፍሪካ ዋንጫ ቀጣይ የጥሎ ማለፍ ጨዋታዎች ከሁለት ቀናት ዕረፍት በኋላ መካሄዳቸውን ይቀጥላሉ።

በይገደብ ዓባይ
2024-01-25