ሀገሬ ቲቪ

ከ70 ሚሊዮን ዶላር በላይ ኢንቨስት የሚደረግበት የክትባት አይነቶችን ለማምረት የሚያስችል የፕሮጀክት ግንባታ ማስጀመሪያና የመሰረት ድንጋይ በቂሊንጦ ኢንዱስትሪ ፓርክ ተቀምጧል።

ከ70 ሚሊዮን ዶላር በላይ ኢንቨስት የሚደረግበት የክትባት አይነቶችን ለማምረት የሚያስችል የፕሮጀክት ግንባታ ማስጀመሪያና የመሰረት ድንጋይ በቂሊንጦ ኢንዱስትሪ ፓርክ ተቀምጧል።

በኢንዱስትሪ ፓርክ የመሰረት ድንጋይ የተቀመጠለት የሺልድቫክስ ኢንተርፕራይዝ ፕሮጀክት ሲሆን እ.አ.አ በ2027 ክትባቶችን የማምረት ተግባር እንዲጀምር ዕቅድ መያዙ ተነግሯል።

ከውጪ የሚገቡ ምርቶችን በሀገር ውስጥ ለመተካት ብሎም የዉጪ ምንዛሪን ለማዳን ፕሮጀክቱ ያለዉ አስተዋፅኦ ከፍተኛ መሆኑን የጤና ሚኒስቴር ሚኒስትር ዶ/ር ሊያ ታደሰ ተናግረዋል።

የኢንዱስትሪ ፓርኮች ልማት ኮርፖሬሽን ዋና ስራ አስፈፃሚ አክሊሉ ታደሰ በበኩላቸዉ ኮርፖሬሽኑ ለሀገር በቀል ኩባንያዎች የሚሰጠዉ ትኩረት ከፍ እያለ መምጣቱን አሳዉቀዉ በተለይም በፋርማሲዩቲካል ዘርፍ ቂሊንጦ ኢንዱስትሪ ፓርክን በመገንባት ለአምራቾች አዘጋጅቷል ብለዋል።

በፕሮግራሙ ላይ በኢፌዲሪ የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የጤና፣ ባህልና ስፖርት ቋሚ ኮሚቴ ሰብሳቢ ወ/ሮ ወርቀሰሙ ማሞ፣ የጤና ሚኒስቴር ሚኒስትር ዶ/ር ሊያ ታደሰ፣ የኢንዱስትሪ ፓርኮች ልማት ኮርፖሬሽን ዋና ስራ አስፈፃሚ አክሊሉ ታደሰ፣ የመንግስት የልማት ድርጅቶች ይዞታና አስተዳደር ዋና ዳይሬክተር አቶ ሀብታሙ ሀይለሚካኤል፣ የአለም ባንክና ሌጆች ተቋማት ከፍተኛ ኃላፊዎች የተለያዩ አምባሳደሮች፣ የጉምሩክ ኮሚሽን አመራሮችና ሌሎች የፌደራልና የክልል አመራሮች ታድመዋል።

በብሩክታዊት አሥራት
2024-01-30