ሀገሬ ቲቪ

ኢትዮጵያ ሙስና ተንሰራፍቶባቸዋል ከተባሉ ሀገራት 98ኛ ደረጃ ላይ ትገኛለች ተባለ።

ኢትዮጵያ ሙስና ተንሰራፍቶባቸዋል ከተባሉ ሀገራት 98ኛ ደረጃ ላይ ትገኛለች ተባለ።

ትራንስፓረንስ ኢንተርናሽናል የተባለው በ180 ሀገራት ያለን የሙስና ሁኔታ የሚያጠና ተቋም በ2023 የፈረንጆች ዓመት ሀገራት በሙስና መለኪያ ያለበትን ደረጃ ይፋ አድርጓል።

ኢትዮጵያ በባለፈው የፈረንጆች ዓመት 2022 ከነበረችበት ደረጃ በአንድ ዝቅ ማለቷን ይኸው የጥናት ቡድን አስታውቋል።

ጥናቱ ካካተታቸው 180 ሀገራት ውስጥ ኹለት ሦስተኛው የሚሆኑት ከ50 በታች ነጥብ ያላቸው እንደሆኑ ያስታወቀው ትራንስፓረንት ይህ በዓለማችን ምን ያህል ሙስና መንሰራፋቱን ያሳያል ብሏል።

በሳምሶን ገድሉ
2024-01-31