ሀገሬ ቲቪ

የቅዱስ ጊዮርጊሱ የፊት መስመር ተጫዋች አቤል ያለው የግብጹን ክለብ ዜድ ለመቀላቀል መስማማቱ ይፋ ሆኗል፡፡

ቅዱስ ጊዮርጊሱ የፊት መስመር ተጫዋች አቤል ያለው የግብጹን ክለብ ዜድ ለመቀላቀል መስማማቱ ይፋ ሆኗል፡፡

በዘንድሮው የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ 8 ግቦችን በማስቆጠር ከፍተኛ ግብ አስቆጣሪው አቤል ያለው የግብጹን ክለብ ዜድ ኤፍሲ ለመቀላቀል ተስማምቷል፡፡

አቤል በ2014 እና 2015 የውድድር ዓመት ከክለቡ ጋር ተከታታይ የሊጉን ዋንጫ ማሳካት ችሏል፡፡

በዘንድሮው የውድድር ዓመትም በርካታ ግቦችን በማስቆጠር ልዩ ብቃቱን አሳይቷል፡፡

የግብጹ ክለብ ዜድ ኤፍሲ በዘንድሮው የውድድር ዘመን ወደ አንደኛ ዲቪዚዮን በማደግ ሊጉን እየመራ ይገኛል፡፡

እራሱንም ለማጠናከር አቤልን ምርጫው አድርጓል፡፡

የዝውውር መስኮቱ ከመዘጋቱ በፊትም አቤልን የግሉ ማድረግ መቻሉ ዛሬ ይፋ ሆኗል፡፡

ይህንንም ተከትሎ አቤል ያለው ከሰልሀዲን ሰይድ፤ ሽመልስ በቀለ፤ ኡመድ ኡኩሪ እና ጋቶች ፓኖም በመቀጠል በግብጽ ፕሪሚየር ሊግ የተጫወተ አምስተኛው ኢትዮጵያዊ ይሆናል፡፡

በይገደብ ዓባይ
2024-02-01