ሀገሬ ቲቪ

የመንገድ መሰረተ- ልማት ችግር ምርት ለማቅረብ ፈተና ኾኖብናል ሲሉ አርሶ አደሮች ተናገሩ።

የመንገድ መሰረተ- ልማት ችግር ምርት ለማቅረብ ፈተና ኾኖብናል ሲሉ አርሶ አደሮች ተናገሩ።

የመንገድ መሰረተ- ልማት ባለመኖሩና በወቅቱ ባለመጠገኑ የምናመርተውን ምርት ለማዕከላዊ ገበያና በተለያዩ የሀገሪቱ ክፍሎች ለሚገኙ የገበያ ማዕከላት ማቅረብ አልቻልንም ሲሉ የከንባታ እና የሃዲያ ዞን አርሶ-አደሮች ቅሬታቸውን ገለጹ።

አርሶደሮቹ ቅሬታቸውን የገለጹት የግብርና ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል የመስክ ምልከታ ባደረገበት ወቅት ነው።

በሃዲያ ዞን እና በከንባታ ዞኖች በክላስተር አትክልት እና ስንዴ በስፋት ቢመረትም በመሰረተ ልማት ምክንያት ወደ ገበያ መድረስ አለመቻሉን ቋሚ ኮሚቴው ከገበሬዎች መታዘቡን አስታውቋል።

በወንድማገኝ አበበ
2024-02-01