የኢትዮጵያ የክፍያ መንገዶች ኢንተርፕራይዝ በ2016 በጀት ዓመት የመጀመሪያ ስድስት ወራት ከ271 ሚሊዮን ብር በላይ አትርፌያለሁ አለ።
ይህ ገቢው ከባለፈዉ ዓመት ተመሳሳይ ወቅት ጋር ሲነጻጸር 27 ነጥብ 8 በመቶ ብልጫ እንዳለው አስታውቋል።
የኢንተርፕራይዙ የ2016 በጀት ዓመት የመጀመሪያዉ ስድስት ወራት የትርፍ አፈፃፀም ከዕቅዱ ጋር ሲነጻጸርም 111 በመቶ ድርሻ እንዳለው ነው የገለጸው።
በብሩክታዊት አሥራት
2024-02-02
