በአማራ ክልል ላይ የተጣለው የአስቸኳይ ግዜ አዋጅ ላይ እየተመከረ ነው፡፡
የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት በአማራ ክልል ላለፉት 6 ወራት የቆየውን የአስቸኳይ ግዜ አዋጅ ላይ በዝግ እየመከረ ይገኛል።
በኢትዮጵያ አማራ ክልል የተፈጠረውን ግጭት ተከትሎ ምክር ቤቱ ነሐሴ 08 ቀን 2015 ዓ.ም የአስቸኳይ ግዜ አዋጅ ማወጁ ይታወሳል።
ለ6 ወራት የቆየው የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ ጥር 8 2016 ዓ.ም. ያበቃ ሲሆን ዛሬ ይህንን አዋጅ ምክር ቤቱ ስብሰባ እያደረገ መሆኑን ሀገሬ ቴሌቪዥን ከስፍራው የደረሰን መረጃ ያሳያል።
በሳምሶን ገድሉ
2024-02-02
