
የሴኔጋል ፓርላማ የሀገሪቱ ፕሬዝዳንታዊ ምርጫ ይራዘም የሚለዉን ሃሳብ አጸደቀ።
የምዕራብ አፍሪካዊቷ ሀገር ሴኔጋል ፓርላማ፤ ከቀናት በፊት የሀገሪቱ ፕሬዝዳንት ማኪ ሳል በዚህ ወር መጨረሻ እንዲደረግ ቀጠሮ ተይዞለት የነበረዉ ምርጫ እንዲራዘም ያቀረቡትን ሃሳብ ማጽደቁ ተነግሯል።
የሴኔጋል ፓርላማ ሀሳቡን በ105 የድጋፍ ድምፅ እና በአንድ ተቃዉሞ፤ ህዳር 15 ድረስ ምርጫዉ ተራዝሞ እንዲቆይ መወሰኑን ቲ.አር.ቲ አፍሪካ ዘግቧል።
ማኪ ሳል፤ የሀገሪቱ ብሄራዊ ጠቅላላ ጉባዔ እና ህገ መንግስታዊ ፍርድ ቤት በእጩዎች ዙሪያ አለመግባባት ዉስጥ በመሆናቸዉ ለየካቲት 25 ተይዞ የነበረዉ ምርጫ ላልተወሰነ ጊዜ መራዘሙን ማሳወቃቸዉ ያታወሳል።
በበላይሁን ፍስሐ
2024-02-06