ሀገሬ ቲቪ

ፖላንድ፤ ከሩሲያና ቤላሩስ ጋር በምትዋሰንበት ድንበር ላይ አዲስ ምሽግ ገንብታለች ተባለ፡፡

ፖላንድ፤ ከሩሲያና ቤላሩስ ጋር በምትዋሰንበት ድንበር ላይ አዲስ ምሽግ ገንብታለች ተባለ፡፡

የሩሲያና ዩክሬን ጦርነት ከተጀመረ ወዲህ፤ ለዩክሬን በርካታ ድጋፎችን እያደረገች የምትገኘዉ ፖላንድ ከሩሲያ ጋር ውጥረት ውስጥ ገብታለች፡፡

አገሪቱ ይህን ተከትሎ ከሩሲያና ቤላሩስ ጋር በምትዋሰንበት ድንበር ላይ አዲስ ምሽግ መገንባቷን አናዶሉ ዘግቧል። የፖላንድ መከላከያ ሚኒስቴር ዩክሬን ጦርነቱን የምትሸነፍ ከሆነ፤ ፑቲን ሌሎች የኔቶ አባል ሀገራት ላይ ጥቃት ለመፈጸም ዉሳኔ ሊያሳልፉ የሚችሉበት ዕድል ይኖራል ብለዋል።

የሀገሪቱ መከላከያ ሚኒስትሩ ዝርዝር መረጃዎችን ከመስጠት ቢቆጠቡም፤ ያሉትን ምሽጎች የማሻሻልና አዳዲስ ምሽጎችን የመገንባት ሂደቱ ተጠናክሮ እንደሚቀጥል መናገራቸው ተገልጿል።

በበላይሁን ፍስሐ
2024-02-06