ሀገሬ ቲቪ

ዕለቱን ከታሪክ ማህደር

በፈርንጆቹ 1821 ልክ በዛሬዋ ዕለት ሳሙኤል ረስት የዋሽንግተንን የእጅ የህትመት ማሽን የፈጠራ ባለቤትነት መብት የተጎናጸፈባት ዕለት ናት።

ዋሽንግተን የህትመት ማሽን በኒው ወርክ በፈረንጆች በ1820ዎቹ በሳሙኤል ረስት እንደተፈለሰፈ የታሪክ ድርሳናት ያወሳሉ። ማተሚያው በጣም ከባድና ግዙፍ ቢሆንም እነደ ዘመኑ ሲታይ ጥሩ ጅምር ነበር ብሎ መውሰድ ይቻላል።

ማተሚያው ከዘመኑ ቀድመው እንደነበሩት ማተሚያዎች በእንጨት ሳይሆን በብረት የተሰራ እንደነበር ይነገራል። ከቀደምቶቹ ማተሚያዎች በተለየ መልኩም በቀላሉ ከቦታ ቦታ ማነቀሳቀስ ይቻላል። መልሶ ሊገጣጠም ስለሚችል በእዝያ ዘመን ገበያውም የሚፈልገው ነበር።

ይህ ማተሚያ በ1938 በዋሽንግተን በመንግስት ቢሮ ውስጥ ጥቅም ላይ ውሏል። የዋሽንግተን ፕሬስ በጣም ተወዳጅ ከመሆኑ የተነሳ ሌሎች የዘመኑ አምራቾች ለመቅዳት ሞክረዋል ግና ሊሳካላቸው አልቻለም ።

ረስት አወዛጋቢ ነው ብለው ብዙዎች በሚስማሙበት ሁኔታ በ1835 አር ሆው በተሰኘው ኩባንያ ቦታውን ተነጥቋል። ለዓመታት ረስት በኒውዮርክ ላይ የተመሰረተውን የህትመት ማሽን አምራች የፈጠራ ባለቤትነት መብቱን ለመሸጥና አሳልፎ ለመስጠት አሻፈረኝ ብሎ ቆይቷል።

ረስት በመጨረሻም በአቋም መዝለቅ አልቻለም። በፈርንጆቹ 1835 የራሱን ኩባንያ ለማቋቋም በማለም ከፍተኛ የእጅ ባለሙያ መስሎ ለሆይ ሰራተኛ ለመሸጥ ተስማማ ።

ኩባንያው እነዚህን ማተሚያዎች እስከ ሃያኛው ክፍለ ዘመን መጀመሪያ ድረስ አምርቷል፣ በኒውዮርክ ያለው ፋብሪካ ከ2,500 በላይ ሰራተኞችን እና ለንደን ላይ ያለው ፋብሪካ ደግሞ 800 ያህል ሰራተኞችን ይዞ እንደነበር ይነገራል። ከ1835 እስከ 1902 ድረስ አር ሆው ከእነዚህ ማተሚያዎች ከ6,000 በላይ ሸጧል።

ለመጨረሻ ግዜ የተሠራው የህትመት ማሽን ዛሬ በሙዚየሞችና ኤግዚቢሽኖች በበርካቶች ይጎበኛል።

ወደ ሀገራችን መለስ ስንል ደግሞ ጥንታዊ ኢትዮጰያውያን ሊቃውንት የሚጽፏቸው መጻሕፍት ለሕዝብ የሚቀርቡት ብራና ተፍቆ ፣ ቀለም ተቀምሞ በእጅ ተፅፎ ነበር።

በዳግማዊ ምኒልክ ዘመነ-መንግሥት የተጀመረው የዘመናዊ ሕትመት ሥራ በሀገሪቱ ቁጥራቸውና መጠናቸው በርከት ያሉ ጋዜጦች፣ መፅሔቶች፣ መጻሕፍት፣ እንዲሁም ሌሎች የሕትመት ውጤቶች መታተም በመጀመራቸው የትምህርትና የሥልጣኔ መሰፋፋት ላይ የበኩሉን ሚና መጫወት እንደጀመረ የዘርፉ ምሁራን ያስረዳሉ።

በመቅደስ እንዳለ
2022-05-13