ሀገሬ ቲቪ

የየካቲት 12 መታሰቢያ በአዲስ አበባ ከተማ በዛሬው ዕለት ታስቧል።

የየካቲት 12 መታሰቢያ በአዲስ አበባ ከተማ በዛሬው ዕለት ታስቧል።

87ኛው የየካቲት 12 መታሰቢያ መርሐ ግብር በአዲስ አበባ ስድስት ኪሎ የሰማዕታት ሃውልት በዛሬው ዕለት ታስቧል።

የፋሺስት ጣልያን ወታደሮች ያደረሱትን አስከፊ ጭፍጨፋ በማሰብ ከፍተኛ የመንግሥት ኃላፊዎች በተገኙበት በ6 ኪሎ የሰማዕታት ሃውልት ስር የአበባ ጉንጉን በማስቀመጥ አክብረዋል።

በሰማዕታት መታሰቢያ በዓሉ ደማቸውን ለሃገር ክብር ላፈሰሱ፣ አጥንታቸውንም ለሕዝብ ነጻነት ለከሰከሱ ጀግኖች ሰማዕታት ክብር መስጠት እንደሚገባ በሁነቱ ተነስቷል።

ከዛሬ 87 ዓመት በፊት ከ30 ሺህ በላይ የአዲስ አበባ ከተማ ነዋሪዎች በጣሊያን ጦር አስከፊ ጭፍጨፋ ማድረጉ ይታወሳል።

በወንድማገኝ አበበ
2024-02-20