በአበባ እርሻና በኢንዱስትሪዎች ለሚሠሩ ሠራተኞች አነስተኛ የደመወዝ ወለል ለማስቀመጥ የሚረዳ ቦርድ ተቋቁሞ ወደ ሥራ ሊገባ መሆኑን የኢትዮጵያ አሠሪዎች ኮንፌዴሬሽን አስታወቀ።
አነስተኛ የደሞዝ ወለል ማለት የመቀጠሪያ መነሻ ደመወዝን እንጂ በሥራ ላይ ያሉትንና በኅብረት ድርድር መሠረት በዓመትና በሁለት ዓመት ክፍያቸው የሚጨመርላቸውን ሠራተኞች እንደማይመለከት መሆኑ ተነግሯል።
የአነስተኛ ደመወዝ ወለልን ተግባራዊ ለማድረግ የቆላ፣ የደጋና የወይና ደጋ አካባቢዎች ሠራተኞችን እንደ አካባቢው ሁኔታ ክፍያቸውን ማጥናትና አስፈላጊ መሆኑም ተመላክቷል።
የአሠሪዎች ኮንፌዴሬሽን አነስተኛው የደመወዝ ወለል ቀርቦ በቅርቡ ሥራ ላይ እንዲውል ከሚመለከታቸው አካላት ጋር በተግባቦት እየተሠራ እንደሚገኝ ፕረስ ድርጅት ዘግቧል።
በብሩክታዊት አሥራት
2024-02-21
