የመንግሥት የፀጥታ ኃይሎች በአማራ ክልል ከፍርድ ውጪ ንፁኃን ዜጎችን እየገደሉ መሆኑን አምነስቲ ኢንተርናሽናል ዛሬ ባወጣው ሪፖርት አስታውቋል።
ቤተሰቦቻቸው የተገደሉባቸው ዜጎች አስከሬን አንስተው ለመቅበር መከልከላቸውንም በሪፖርቱ ገልጿል።
ሰላማዊ ዜጎቹ የተገደሉት የታጠቁ ኃይሎችን ትደግፋላቸሁ ተብለው እንደሆነ ተነግሯል።
በተጨማሪም በአማራ ክልል ያለው የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ፣ የኢንተርኔት መዘጋት እንዲሁም አንድ አንድ አካባቢዎች ላይ የመገናኛ ዘዴዎች ላይ እገዳ በመጣሉ የመናገር ነፃነትን የገደበ እንዲሁም የሰብአዊ ጥሰቱ እንዲባባስ እያደረገ መሆኑ ተጠቁሟል።
በአማራ ክልል ባለው የፀጥታ ችግር ምክንያት እየተፈፀመ ያለውን የሰብአዊ ጥቃት በገለልተኛ ወገን እንዲመረመር መንግሥት እንዲፈቅድ የአምነስቲ ኢንተርናሽናል የምስራቅና የደቡብ አፍሪካ ክልላዊ ዳይሬክተር ታይገር ቻጉታህ ጠይቀዋል።
በይስሃቅ አበበ
2024-02-26
