ሀገሬ ቲቪ

አሜሪካ የኢትዮጵያ የባህር በር ጥያቄ ተገቢነት ያለው ነው አለች።

አሜሪካ የኢትዮጵያ የባህር በር ጥያቄ ተገቢነት ያለው ነው አለች።

የኢትዮጵያ የባህር በር የማግኘት ያቀረበችው ጥያቄ ተገቢነት ያለው ቢሆንም ከሶማሊያ መንግሥትና ከአጎራባች አገሮች ጋር መነጋገር ላይ በተመሰረተ አካሄድ ሊሆን እንደሚገባ የአሜሪካ የአፍሪካ ጉዳዮች ረዳት ኃላፊ ሞሊ ፊ አስታውቀዋል ሲል ሪፖርተር ዘግቧል፡፡

ኃላፊው ከሁለቱ መሪዎች ጋር ባደረጉት ቆይታ የሶማሊያን ሉዓላዊነትና የግዛት አንድነትን በማክበር ላይ በመመሥረት ችግሩ እንዲፈታና ውጥረቱ እንዳይባባስ ማሳሰባቸውን ተናግረዋል፡፡

የሶማሌላንድ ጉዳይ መፈታት ያለበት በሶማሊያና በሶማሌላንድ ሕዝብ እንጂ በውጭ ተዋናዮች አይደለም ያሉት ሞሊ ፊ፤ ቀጣናው ውስጥ ካለው በተጨማሪ ግጭትን ማስተናገድ አይገባም ብለዋል፡፡

በናርዶስ ታምራት
2024-02-26