ሀገሬ ቲቪ

ጠቅላይ ሚኒስትር አቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ወደ ኬንያ ሊያቀኑ ነው።

ጠቅላይ ሚኒስትር አቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ወደ ኬንያ ሊያቀኑ ነው።

ጠቅላይ ሚኒስትር አቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ወደ ናይሮቢ እንደሚያቀኑ ከዲፕሎማቲክ ምንጮች ሰምቻለሁ ሲል ኔሽን የተሰኘው ጋዜጣ በመካነ ድሩ አስነብቧል።

ይህ የጠቅላይ ሚኒስትሩ ይፋዊ የሥራ ጉብኝት ፕሬዝዳንት ዊሊያም ሩቶ ከተመረጡ ወዲህ ለመጀመሪያ ግዜ ነው ተብሏል።

የጠቅላይ ሚኒስትር አቢይ ጉዞ ሁለቱ ሀገራት በቀጠናዊ እና አህጉራዊ ጉዳዮች ላይ ያላቸውን መተባበር እንደሚያጠነክረው ዘገባው ጨምሮ አስታውቋል።

በሳምሶን ገድሉ
2024-02-26