ሀገሬ ቲቪ

አፍሪካውያን የሚሳተፉበት አሜሪካ-መራሽ አህጉራዊ ወታደራዊ ልምምድ ሊካሄድ ነው።

አፍሪካውያን የሚሳተፉበት አሜሪካ-መራሽ አህጉራዊ ወታደራዊ ልምምድ ሊካሄድ ነው።

25 የአፍሪካ ሀገራት የሚሳተፉበት አሜሪካ-መራሽ አህጉራዊ ወታደራዊ ልምምድ ኬንያ ውስጥ በዛሬው ዕለት እንደሚጀመር የኬንያ መገናኛ ቡዙኃን ዘግበዋል፡፡

ወታደራዊ ልምምዱ ለ10 ቀናት የሚቆይ እንደሆነ ተነግሯል፡፡

ልምምዱ ላይ ከአንድ ሺ በላይ ወታደሮች ይሳተፉበታል ተብሏል፡፡

የወታደራዊ ልምምዱ አላማ የተሳታፊ ሀገራት ወታደሮች በተባበሩት መንግሥታት ድርጅት እና አፍሪካ ኅብረት የሰላም ማስከበር ተልዕኮዎች በብቃት እንዲሠማሩና ለተፈጥሯዊ ቀውሶች በቂ ምላሽ እንዲሰጡ አቅማቸውን ለመገንባት ነው ተብሏል።

በወንድማገኝ አበበ
2024-02-26