ሐማስ ታጋቾችን እንዲለቅ እና በጋዛ ተኩስ እንዲቆም የሚመክረው ውይይት ተስፋ ሰጪ ነው ተባለ።
በእስራኤል እና በሐማስ ጦርነት የማቆም እና ታጋቾችን በመልቀቅ ላይ እየመከረ የሚገኘው የፈረንሳይ ፓሪስ ውይይት ተስፋ ሰጪ ሊሆን ይችላል ተባለ።
የአሜሪካ ብሔራዊ ደሕንነት አማካሪ ጄክ ሱሉቫን ለሲኤንኤን እንዳስታወቁት በፓሪስ በተካሔደው ውይይት የእስራኤል፣ አሜሪካ፣ ግብጽ እና የኳታር ተወካዮች የተኩስ አቁም እና ታጋቾች በሚለቀቁበት ሁኔታ ላይ ከመግባባት መድረሳቸው ተነግሯል።
በዝርዝር ጉዳዮች ላይ ገና ድርድር እየተካሔደ መሆኑን የገለጹት ጄክ ሱሊቫን ግብጽ እና ኳታር ከሐማስ ጋር እንደሚወያዩ ተነግሯል።
የእስራኤል ጠቅላይ ሚኒስትር ቤኒያሚን ኔታንያሁ ግን እየተካሔደ የሚገኘው ውይይት ታጋቾችን የሚያስለቅቅ ሥምምነት ላይ ስለመድረሱ እርግጠኛ አለመሆናቸውን ተናግረዋል።
በወንድማገኝ አበበ
2024-02-26
