ሀገሬ ቲቪ

ቤንሻንጉል ጉምዝ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ አሻድሊ ሀሰን የተለያዩ ሹመቶችን ሰጡ።

ቤንሻንጉል ጉምዝ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ አሻድሊ ሀሰን የተለያዩ ሹመቶችን ሰጡ።

የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ አሻድሊ ሀሰን ለተለያዩ የኃላፊነት ቦታዎች ሹመት መስጠታቸው ተገለፀ።

በዚህም አቶ አስር ኢብራሂም የክልሉ ንግድና ገበያ ልማት ቢሮ ኃላፊ አድርገው ሲሾሙ አቶ አልጀሊ ሙሳ የክልሉ ሚዲያ ዋና ዳይሬክተር አድርገው ሾመዋል።

በተጨማሪም አቶ ብርሃኑ አየሁ የርዕሰ መስተዳድር የሕግ አማካሪ እንዲሁም አቶ በቀለ አንበሳ የርዕሰ መስተዳድር የኢኮኖሚ አማካሪ ሆነው ተሹመዋል ተብሏል።

አቶ አስማማው አብሾክ የክልሉ ፍትህ ቢሮ ምክትል ቢሮ ኃላፊ፣ አቶ አብዱልከሪም ሙሳ በክልሉ ግብርና ቢሮ የተፈጥሮ ሃብት ልማት ዘርፍ ምክትል ቢሮ ኃላፊ፣ አቶ ሉቁማን አብዱልቃድር የአካባቢ ደን ሀብት ጥበቃ አየር ንብረት ለውጥ ባለስልጣን፣ አቶ ሁሴን ሐሰን በኢንዱስትሪና ኢንቨስትመንት ቢሮ የኢንቨስትመንት ዘርፍ ምክትል ቢሮ ኃላፊ እንዲሁም አቶ አህመድ ሙሳ በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል የአሶሳ ዞን ምክትል ዋና አስተዳዳሪ ሆነው መሾማቸውን ከክልሉ ኮሙዩኒኬሽን ጉዳዮች ቢሮ ማህበራዊ ትስስር ገፅ ተመልክተናል።

በፂዮን ታደሰ
2024-02-26