የኢትዮጵያ አየር መንገድ ወደ ደምቢ ዶሎ መደበኛ በረራ ጀመረ።
የኢትዮጵያ አየር መንገድ ለዓመታት ተቋርጦ የቆየውን ከአዲስ አበባ ወደ ደምቢ ዶሎ የሚደረግ መደበኛ በረራውን በዛሬው ዕለት የካቲት 18 ቀን 2016 ዳግም መጀመሩን አስታወቀ።
በዛሬው ዕለት የተጀመረው በረራም በሳምንት ሶስት ጊዜ የሚደረግ መሆኑ የተነገረ ሲሆን በሁለተኛው ወር ደግሞ በሳምንት ወደ ሰባት ጊዜ ከፍ እንዲል መግባባት ላይ መደረሱን አዲስ ስታንዳርድ ዘግቧል።
ወደ ደምቢ ዶሎ የሚደረገው በረራ በአካባቢው በተፈጠረው የጸጥታ ችግር ምክንያት ተቋርጦ መቆየቱ ይታወሳል።
በብሩክታዊት አሥራት
2024-02-26
