የለሚ ናሽናል ሲሚንቶ ፋብሪካ ምርት ማምረት ሊጀምር ነው።
ግዙፉ ለሚ ናሽናል ሲሚንቶ ፋብሪካ በቅርቡ ተመርቆ ምርት ማምረት እንደሚጀምር የአማራ ክልል ርእሰ መሥተዳድር ጽሕፈት ቤት አስታወቀ።
ፋብሪካው በአፍሪካ ግዙፉ የሲሚንቶ ፋብሪካ ሲሆን በቀን ከ10 ሺ ቶን በላይ ሲሚንቶ የማምረት አቅም ያለው መሆኑ ተነግሯል።
ፋብሪካው በሙሉ አቅሙ ወደ ሥራ ሲገባ በቀን ከ130 ሺ እስከ 150 ሺ ኩንታል ሲሚንቶ ያመርታል ተብሎም ይጠበቃል ተብሏል፡፡
ግንባታው ተጠናቆ ምርት ማምረት ሲጀምር የኢትዮጵያን የሲሚንቶ ፍላጎት 50 በመቶ መሸፈን የሚችልም መሆኑ ተመላክቷል።
ፋብሪካው በአማራ ክልል ሰሜን ሽዋ ዞን እንሳሮ ወረዳ ለሚ ከተማ የተገነባ ግዙፍ የሲሚንቶ ፋብሪካ ነው።
በብሩክታዊት አሥራት
2024-02-27
