የፈረንሳዩ ፕሬዝዳንት ኢማኑኤል ማክሮን በሩሲያና ዩክሬን ጦርነት ለዩክሬን የሚሰለፉ ወታደሮችን ለመላክ የሚያስችል ስምምነት ባይኖርም የሚከለክል ሁኔታ እንደማይኖር ገልጸዋል፡፡
ማክሮን አስተያየታቸውን የሰጡት 20 የሚሆኑ የአውሮፓ ሀገሮች በሩሲያ ዩክሬን ጦርነት ዙሪያ ለመምከር በፓሪስ በተገናኙበት ወቅት ነው።
ሩሲያ ጦርነቱን እንዳታሸንፍ ያለብንን ሁሉ እናደርጋለን ያሉት ማክሮን የሩሲያ ሽንፈት ለአውሮፓ ሀገራት ደህንነት እና መረጋጋት አስፈላጊ እንደሆነ እናምናለን ብለዋል።
ሆኖም የትኞቹ ሀገራት ወታደሮቻቸውን ወደ ዩክሬን ለመላክ ሀሳብ እንዳቀረቡ ግልፅ የሆነ መረጃ አልሰጡም ሲል ሮይተርስ ዘግቧል።
በፂዮን ታደሰ
2024-02-27
